የሀረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራም 3ተኛ ምእራፍ በማስመልከት ውይይት አካሂዷል፡፡
ቢሮው ለአሚር ኑር እና ጅኔላ ወረዳ ማህበራዊ ተጠያቂነት ላይ ለተ አፈፃፀሞች ምስጋና አቅርቧል፡፡
የሐረሪ ክልል ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ አሚር ኑር እና ጅኔላ ወረዳ ማህበራዊ ተጠያቂነት ዙሪያ በመድረኩ በተሰሩ አፈፃጸሞች ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡
ንግግር ያደረጉት የቢሮው ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ካሊድ አብዲ የማህበራዊ ተጠያቂነት መርሃ ግብር በኢትዮጵያ መንግስትና በአለም ልማት ማህበር መካከል በተደረገ ስምምነት በተገኘ ድጋፍ እየተተገበረ ያለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በፕሮግራሙ በመንገድ፣ በውሃ፣መብራት በትምህርት እና በሌሎች ዘርፎች የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ገልጸዋል፡፡
በልማት በኩል ጠያቂ ህብረተሰብ መፍጠር ወሳኝ ነው ያሉት ም/ ሀላፊው ቢሮው እስከ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ በትምህርት ቤቶች ውስጥ የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት ቀርቧል፡፡
በጀግኖችና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶቸ ውስጥ በውሃ አቅርቦት መንገድ ማመቻቸት መፀዳጃ ቤት በመስራት ለተደረገው አስተዋፅኦ በሪፖርቱ ወቅት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ትምህርት ቤቶች እድሳት እና የተማሪዎች ምገባ ላይም እየተሰራ መሆኑንም በሪፖርቱ ተገልፃል፡፡
የመድረኩ ተሳታፊዎች በትምህርት ቤቶች የመሰረተ ልማት ማስፋፋት ላይ የተሰራው ስራ ህብረተሰቡ መሰረት ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራም የተለያዩ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ወረዳዎችና ተቋማት የምስጋና ወረቀት ተሰጥቷል፡፡
Harari mass media agency