የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ አመራርና ሰራተኞች 18ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን “ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በፓናል ውይይት አከበሩ ፡፡
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ሃላፊ አቶ መሐመድ ያህያ በየዓመቱ ህዳር 29 የሚከበረው የኢትየጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል በብሔረሰቦች መካከል በብዝኃነት ላይ የተመሰረተ ህብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲዳብር በማድረግ ሀገራዊ አንድነትን ማፅናት የሁላችንም ተግባር ነው ብለዋል፡፡
በቢሮው ምክትል ሃላፊ የሆኑት አቶ አብዱልባሲጥ አቡበከር ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሀገር እንደሆነችና በአንድ ሀገር ላይ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች መኖራቸው የብዝሐነት መገለጫ መሆኑን ይህም በአግባቡ ከተያዘ ዜጎች ሁለንተናዊ መብታቸው እንዲከበር፤ በጋራ በመቆምም እንዲሰሩ፤ ሀገራቸውን በጋራ እንዲያገለግሉ ጉልበት አቅም ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ተሳታፊዎችም ሁላችንም በተሰማራንበት የሥራ መስክ ብቁ ሙያዊ የሥራ ክህሎትን የተላበሱና የሕዝብ አገልጋይ የሆኑ ሙያተኞች በመሆን ህብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጉላት፣ ልዩነቶችን በማጥበብና ሀገራዊ አንድነትን ማጽናት የሁላችንም ጥረትና ፍላጎት ሊሆን ይገባል ሲሉ በውይይታቸው አንስተዋል።
በተጨማሪም በአለም አቀፍ ደረጃ ለ32 ጊዜ በሀገራችን ለ18ኛ“መቼም፣ የትም፣ በምንም ሁኔታ ፆታዊ ጥቃትን ዝም አንበል” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የፀረ ፆታዊ ጥቃትን አክብረዋል። የፀረ-ጾታዊ ጥቃት ቀን የሚከበረብት አላማ በሴቶች ላይ የሚፈጸም ማንኛውም አይነት አካላዊ ፣ስነ ልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት የሚያስከትል ጾታን መሰረት ያደረገ የሀይል ጥቃትን ለመቃወም እንደሆነ ተገጿል፡፡
በተጨማሪም “ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው በህብረት እንታገል” በሚል መሪ ቃል አጠር ያለ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበቷል። ሁሉም በተሰማራበት የስራ ዘርፍ የአገልጋይነት ስሜት መላበስ እንደሚገባም ተናግረዋል።