ሀረር የጁገል ቅርስን ውብ እና አረንጓዴ በማድረግ ለነዋሪዎቿ እና ለጎብኚዎች ምቹ እንድትሆን ለማድረግ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል ።
የሀረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ ያህያ የቢሮው አመራሮች በጁገል አለም አቀፍ ቅርስ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ውብና ጽዱ ለማድረግ በቢሮው እየተሰሩ ያሉ የስራ እንቅስቃሴዎች ጎበኝተዋል።
ሀረር ከተማን እንደ ስሟ ውብ ማድረግ ለከተማው ውብት እና ለቱሪዝም ዕድገቱም ያለው ፋይዳ የላቀ በመሆኑ ቢሮው ለማልማት የተረከበውን አካባቢ የፅዳት እና የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን ተገቢውን ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተሰሩ ስለመሆኑ ተመልክተዋል ።
የአለም አቀፍ ቅርጽ የሆነው የጁገል ታሪካዊ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ፅዱ ፣ ውብ እና ለነዋሪዎቹ ምቹ ለማድረግ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል።