በክልሉ ጳጉሜ 3 – የሉዓላዊነት ቀን ተከበረ
በሀረሪ ክልል ጳጉሜ 3 – የሉዓላዊነት ቀን ከጠዋት ጀምሮ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
ዕለቱን “ኅብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት”በሚል መሪ ቃል ነው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በኑር ፕላዛ የሰንደቅ አላማ ስነ ስርዓት በማከናወን ያስጀመሩት።
ዕለቱ የሰንደቅ አላማ ስነ ስርዓትን ጨምሮ በፓናል ውይይት እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ የከተማ እንቅስቃሴዎችን በመግታት በክልሉ ብዙሀን መገናኛ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ብሄራዊ መዝሙር ይለቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።