የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ እድሳት የተደረገለትን የመኖሪያ ቤት አጠናቆ ለባለቤቱ አስረከበ፡፡
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ኻሊድ አብዲ ቤቱን ለአቅመ ደካማ ቤተሰቦች ባስረከቡበት በአሁኑ ወቅት በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት እየተከናወኑ ካሉ የልማት ስራዎች መካከል የሰው ተኮር የልማት እንቅስቃሴ አንዱ ነው ብለዋል።
ይህ የሰው ተኮር ማህበራዊ አገልግሎት በዚህ የሚቆም እንዳልሆነ ጠቅሰው ወደፊትም ቀጣይነት ያለው ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ይህን የመሰለው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ወገን፣ አለኝታና ደጋፊ አለኝ የሚለውን ስሜት ያጠናክራል ብለዋል።
የእርስ በርስ ትስስርን ማጎልበት አንዱ ለሌላው አስፈላጊና ወሳኝ መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን አስገንዝበዋል።
እድሳት የተደርገላቸውን ቤት የተረከቡት አቅመ ደካማ ዜጋ ለተደረገላቸው የቤት እድሳት ምስጋና አቅርበዋል።
ከቤት እድሳቱ በተጨማሪም የአንድ ወር ቀለብና ደብተር በስጦታ ተበርክቶላቸዋል።