የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ አመራርና ሰራተኞች በዛሬው እለት የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሂደዋል፡፡
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ኻሊድ አብዲ እኛ የምንለግሳት ትንሽ ደም ህይወትን ማዳን ስለምትችልና በተለይ በወሊድ ግዜ ደም ፈሷቸው የሚሞቱ እናቶችን ህይወት መታደግ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ከስጦታዎች ሁሉ የላቀ የሆነውን ደም በቋሚነት በየሶስት ወሩ መለገስ በደም እጥረት ምክንያት አንዲትም እናት መሞት እንደሌለባት እንዲሁም በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ለሚደርስ ጉዳት በደም እጥረት የሰው ህይወት ማለፍ ዬለበትም ሲሉ ገልጸዋል ፡፡
ከሀረሪ ክልል ደም ባንክ አገልግሎት የመጡት ባለሞያ ወ/ሮ ኢትዮጵያ በበኩላቸው ፍላጎቱና አቅርቦቱ ተመጣጣኝ ስላልሆነ ህብረተሰቡ ደም ልገሳው ላይ ሊረባረብ ይገባል ብለዋል፡፡
ደም መለገስ ለጋሹ ላይ ምንም አይነት የጤና ችግር የማያስከትል መሆኑን የገለፁት ወ/ሮ ኢትዮጵያ ህብረተሰቡ ያለምንም ስጋት ደም በመለገስ የሌሎች ህይወት መታደግ እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡