የክልሉ ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የ2017 በጀት አመት የበጀት ዝግጅታቸው የሚሰማበትና የሚገመገምበት የበጀት ስሚ ፕሮግራም ተጀምሯል ፡፡
አመታዊ የበጀት ስሚውን ፕሮግራም የመሩት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ሃላፊ አቶ መሐመድ ያህያ የበጀት ስሚውን ሲያስጀምሩ እንደገለጹት የክልሉ ባለ በጀት ተቋማት የመጪው በጀት ዓመት በጀታቸውን ሲያዘጋጁ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ፣የተጠናቁቁትን ስራ ማስጀመር፣ አዲስ ፕሮጅቶችን ጀምሮ መጨረስና ፕሮጀክቶቹ በተቀመጠላቸው መርሃ ግብር መሰረት መጠናቀቃቸውን ታሳቢ ባደረገ መልኩ መዘጋጀት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የበጀት ስሚው ፕሮግራም ዛሬ ሲጀመር በመርሃ ግብሩ መሰረት ትምህርት ቢሮ፣ጤና ጥበቃ ቢሮ፣ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንና የኢንተርፕራይዞች ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮና ሌሎች ተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት አመት የካፒታል ፕሮጀክት እቅዳቸውን አቅርበው አስገምግመዋል።
የበጀት ስሚ መርሀ- ግብሩ ዋንኛ ዓላማ የካፒታል በበጀት ዕቅዱ ውስጥ የሚቀርቡ የወጭ ፍላጎቶች በተመለከተ ካለው የበጀት እጥረት አኳያ በቁጠባና በውጤታማነት ላይ ተመስርተው መዘጋጀታቸውን የወጭ ዕቅዱም ከፊዚካል ስራዎች ጋር ተጣጥሞ የቀረበ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሆነ ተገልጿል።
የ2017 ካፒታል በጀት እቅድ መንግስት ያስቀመጠውን የ10 አመት መሪ የልማት ዕቅድ ያማከለ እና የፕሮጃክቱ ማሟላት ያለበተን መስፈርት ተሟልቶ መቅረብ እንደለበት ተመላክቷል።
በተጨማሪም የካፒታል ፕሮጀክቱ እቅድ ሲዘጋጅ የህዝብን መሰረታዊ ችግር የሚፈታና የህዝቡ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆን እንዳለባቸው ሀሳብ ተነስቷል።
በመጨረሻም በዚሁ መድረክ ከተገኙት ሁሉም የተቋማት የስራ ኃላፊዎች ጋር በቂ የሃሳብ ልውውጥ ከተደረገ በኋላም የተሰጣቸውን ግብአት አካተው የተስተካከለ የበጀት ዕቅዳቸውን በጥቂት ቀናት ውስጥ እንዲያቀርቡ በቢሮ ሃላፊው አቅጣጫ ተሰጥቶ የዕለቱ የበጀት ስሚ መርሃ-ግብር ተጠቃሏል ፡፡
መርሃ ግብሩ በቀጣይ ቀናትም የሚቀጥል መሆኑ ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል።