መንግስት በአለም አቀፍ ከልማት ማህበር ጋር በመተባበር የሚተገበራቸውን የመሰረታዊ አገልግሎቶችና የማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራሞችን የአፈፃፀም ደረጃ ለፕሮግራሞቹ በተቀመጡት ውጤት አመላካች መለኪያዎች አማካይነት ለመለካት ይረዳ ዘንድ በየግማሽ ዓመቱ የጋራ የውይይት መድረክ ይዘጋጃል ።
በመሆኑም በክልላችን ስለ መሰረታዊ አገልግሎቶች አሰጣጥና በማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራሞች ላይ የጋራ ግምገማ (JRIS) የውይይት መድረክ በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ አስተባባሪነት በዛሬው ዕለት በመስክ ምልከታ ተጀምሯል።
በምልከታው የሐኪም ወረዳ መስተዳደር ጽ/ቤት፣የአራተኛ ጤና ጣቢያና የአቦከር 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ ገምግሟል።
በመሰረታዊ ማህበራዊ አገልግሎቶች ማለትም በትምህርትና ጤና ሴክተር ውስጥ ያሉ ቁልፍ አገልግሎት መለኪያ ደረጃዎች ላይ ያሉ ችግሮችና መስተካከል ያለባቸውን ጉዳዮች ተመላክቷል።
በነገው ዕለት በሚካሄደው የጋራ ግምገማ ደህነት ተኮር የተባሉት መሰረታዊ ማህበራዊ አገልግሎት ዘርፎች የሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች በሚያቀርቡት ሪፖርት መሰረት የተከናወኑ ተግባራትን ከእቅዱ አንጻር የሚገመግም ይሆናል፡፡