16ኛው ብሄራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለህብረ-ብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው” በሚል መሪ ቃል ከረፋዱ 4 ሰዓት ተኩል ላይ በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሃላፊ አቶ መሐመድ ያህያ እንደተናገሩት ሰንደቅ ዓላማ የብሔራዊ አንድነት መገለጫ፤ የአንድ ሀገር ዜጎች ሀገራዊ ፍቅርና ብሔራዊ ስሜትን የሚገልፁበት፤ ታሪካዊ ትስስርና ስነ-ልቦናዊ አንድነት የሚንፀበረቁበት የሀገራዊ አንድነትና ህብረት አርማና ምልክት ነው ብለዋል።
በማያያዝ ሰንደቅ ዓላማችን የብዝሃነታችን መገለጫ የሉዓላዊነታችን ምሰሶ ነው በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ ሰንደቅ ዓላማ ክብር በየተሰማራበት የሥራ መስክ ታላቅ ስኬት ማስመዝገብ ይጠበቅበታል ሲሉ ገልፀዋል ።
የዘንድሮው ብሄራዊ የባንዲራ ቀን ስናከብር ሃገራዊ ነባራዊ ሁኔታውን በማገናዘብ የሀገር አንድነትና ሉአላዊ ክብር በሚረጋገጥበት መልኩ በማሰብ መሆኑንም ተናግረዋል።
በመጨረሻ የዕለቱን መልክቶችን በማስተላለፍ፣ሰንደቀ ዓላማ ፊት ቃል መግባትና የባንዲራ መስቀል ስነ-ስርዓት በማከናወን ፕሮግራሙ ተጠናቋል ፡፡