ሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪና ካቢኔያቸው በክልሉ በከተማና በገጠር እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው ።
ከፕሮጀክቶቹ መካከልም የአስፓልት መንገድና የኢኮ ፓርክና መዝናኛ ፕሮጀክት እንዲሁም ወጣቶች የማምረቻና የመሸጫ ሼድ የጉብኝቱ አካል ናቸው።
እንዲሁም የንፁህ መጠጥ እና የመስኖ ግንባታ ፕሮጀክቶች፣ አዳዲስ የገጠር ጠጠር መንገድ ግንባታ ጥገናና ሌሎች ፕሮጀክቶች ይገኙባቸዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንዳሉት በክልሉ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል።
በክልሉ የካፒታል ፕሮጀክቶችን ከፍጻሜ ለማድረስ በጥራት፣ በፍጥነትና በሀላፊነት መስራት ይገባል ብለዋል።
በተለይ በክልሉ የተገነቡት የማምረቻና መሸጫ ሼዶች በአጭር ጊዜ ለኢንቸርፕራይዞች አገልግሎት እንዲሰጡ መደረግ አለበት ብለዋል።
በጉብኝቱም የክልሉ ርዕሰ መስተደድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣፣በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ፣ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሮዛ ኡመርን ጨምሮ ላኪች የሴክተር መስሪያ ቤት ሃላፊዎች ተገኝተዋል።










