የሐረሪ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ዙሪያ ከቢሮው ሰራተኞች ጋር ዉይይት እያካሄደ ይገኛል ::
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ሃላፊ አቶ መሐመድ ያህያ በዉይይቱ መክፈቻ ላይ እንደገለፁት በተቋሙ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በግልጽ በማንሳት ለእያንዳንዱ ችግር ባለቤት በመስጠት በ2017 በጀት አመት የዕቅዳችን አካል በማድረግ ችግሩን መፍታት እንደሚገባ ተገልጿል ::
ቢሮው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመፍታት አንፃር የበተቋሙ የተገልጋይን አቤቱታ እና ቅሬታ አቀራረብ እና አፈታት ስርአት ስለመዘርጋቱ ፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሉ ቅንጅታዊ አሰራሮች እና ሌሎችንም ጉዳዮች ተነስቷል ።
ውይይቱ ከሰዓት መርሃ ግብርም የሚቀጥል ይሆናል ።