የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በ2016 የበጀት አመት የላቀ ዉጤት ላስመዘገቡ ሰራተኞችና ባለድርሻ አካላት የእዉቅና እና ሽልማት ፕሮግራም አካሄደ፡፡
በዛሬው ዕለት በተካሄደዉ የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር በበጀት አመቱ በስራቸዉ ጥሩ የስራ መንፈስ በመፍጠር ዉጤታማ የሆኑ የስራ ክፍሎችና ሰራተኞች የሰርተፊኬትና የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተላቸዉ፡፡
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ሃላፊ አቶ መሐመድ ያህያ በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ እንዳሉት የዚህ የእዉቅና እና ሽልማት ዋንኛ ዓላማ በሰራተኞች እና በስራ ክፍሎች መካከል የዉድድር መንፈስ በመፍጠር ለተሻለ ስራ እንዲተጉ ማድረግ ሲሆን በተጨማሪም በዚህ ሂደት ዉጤታማ ለሆኑ የእዉቅና እና ማበረታቻ መስጠት ነዉ ብለዋል፡፡
ለተገልጋዮቻችን የምንሰጠዉ አገልግሎት መሻሻል እንደተጠበቀ ሆኖ አሁንም ከዚህ በበለጠ በተሰማራንበት የስራ ዘርፍና በተነሳሽነት መንፈስ ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡
በመጨረሻም ለተቋሙ ዕቅድ ክንዉን መሳካት የበኩላቸዉን ኃላፊነት ለተወጡ ዳይክተሮችና ሰራተኞች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በዘንድሮ አመት ከቢሮው ጋር ባላቸው የስራ ቁርኝት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ለክልሉ ሴክተር መስሪያ ቤትና ወረዳዎች የማበረታቻ ሰርፊኬት ተሰጥቷል፡፡