የሀረሪ ክልል ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በአሚር ኑር ወረዳ የማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራም ማስጀመሪያና ግንዛቤ መፍጠሪያ የውይይት መድረክ አካሂዷል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የቢሮው የቻናል አንድ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ኑረዲን መሀመድ መሰረታዊ የአገልግሎት ዘርፎች ውሃ፣ትምህርት ፣ጤና ፣ግብርና እና በመሳሰሉት የህብረተሰብ ፍላጎትና ስራዎች ስለመጣጣማቸው በየግዜው ክትትል በማድረግ ማስተካከያ እንዲወሰድ ፕሮግራሙ ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑንና ህብረተሰቡም በዘርፉ ያለው ግንዛቤ እንዲሻሻል ያደርጋል ብለዋል፡፡
የማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራም የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት ተሳትፎ ዜጎች የልማቱ ቀጥተኛ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከዕቅድ ዝግጅት እስከ ትግበራው በንቃት እንዲሳተፉ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጥ በተፈለገው ደረጃ ለማሳደግ የሚመለከታቸው ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተገልጿል ።
ፕሮግራሙ ቀደም ሲል በጂኔላ ወረዳ ተግባራዊ ሆኖ ውጤት ማስመዝገባቸውን የገለፁት አቶ ኑረዲን አሁን አሚር ኑር ወረዳ ላይ ተግባራዊ ለማድረግ የማስተዋወቅ መድረክ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።
በመድረኩ የሴቶችና ወጣት አደረጃጀቶች፣ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላትም ተሳትፈዋል ።
ተስፋ ለህፃናት ድርጅት በዘርፉ በክልሉ እየሰሩ ያሉትን ስራ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን የጅኔላ ወረዳም ፕሮጀክቱ በወረዳው ተግባራዊ በሆነበት ግዜ የነበረውን ተሞክሮ አጋርተዋል ፡፡
በፋይናንስ ግልፀኝነት እና ተጠያቂነትና ፕሮጀክት አፈጻጸም ዙሪያ ግንዛቤ ተሰጥቷል፡፡
ባጠቃላይ በቀረቡት ገለፃዎች ላይ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያቶች የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የቻናል አንድ አስተባባሪ አቶ ኑረዲን መሐመድ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።