በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት ፕሮግራም አዘጋጅነት ለአሚር ኑር ወረዳ መስተዳድር ለተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በበጀት ምንነት ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል
የፋይናንስ ግልፅነት ሥርዓት ማስፈን ከሚሰጣቸው ጠቀሜታዎች መካከል አንዱ ዜጎች በየአካባቢአቸው የተመደበላቸውን የበጀት መጠን እና የሚሠሩ ሥራዎችን አውቀው አፈጻጸሙ ምንድን ነው ብሎ የሚጠይቅ ጠያቂ ማህበረሰብ እንዲኖር ያግዛል ተብሏል ።
የመንግሥትን ሀብት በአግባቡ ሥራ ላይ ለማዋል፣መንግሥት ህዝቡን የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ በተለያየ ዘርፍ የሚመደበውን በጀት ውጤታማና በአግባቡ ተግባራዊ ከማድረግ ባለፈ በየአስተዳደር እርከኑ የሚካሄዱ ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች ያስገኙትን ፋይዳ በግልጽ ለህብረተሰቡ ማሳወቅ አስፈላጊ ነው።
በክልሉ መንግሥት የሚመደበው በጀት ለታለመለት ዓላማ በአግባቡ ሥራ ላይ መዋሉ መከታተልና የሚስተዋሉ የአፈጻጸም ችግሮችንም ለይቶ በማወቅ የመፍትሔ አቅጣጫ ማስቀመጥ ከያንዳንዱ የህዝብ ተወካዮችና በመስኩ ከተሠማሩ የፋይናንስ አመራሮችና ባለሙያዎች የሚጠበቅ ተግባር ነው ያሉት የገንዘብ ኢኮኖሚ ትብበር ቢሮ የፋይናንስ ግልፅነትና ተጠያቂነት ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ኢሊያስ ጂብሪል ውስን የሆነውን በጀት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ መጠቀምና በስራ ላይ ስለመዋሉ የሚገነዘብ ህብረተሰብ መፍጠር ተቀዳሚ ተግባር እንደሆነ ገልፀዋል።
በበመንግስት በጀት ዙሪያ የተዘጋጀው ይህ መድረክ ዋና ዓላማው በየአካባቢው የሚከናወኑ ማናቸዉም ተግባራት የመንግስት በጀትና አጠቃቀም ሁኔታዎች በግልፀኝነትና ተጠያቂነት መርህ ተግባራዊ መሆን እንዳለባቸው ገልፀዋል፡