Harari BoFEC
No Result
View All Result
  • ዋና ገፅ
  • ቢሮው
    • ስለ እኛ
    • የቢሮ ሃላፊው መልዕክት
    • የስራ ክፍሎች
  • ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች
    • የቻናል አንድ ፕሮግራም
    • የተቀናጀ የበጀትና የወጪ መረጃ ሥርዓት (IBEX)
    • የፋይናንስ ግልፅነትና ተጠያቂነት (FTA)
  • ሰነዶች
  • ሚዲያ
    • አምዶች
    • የፎቶ አምዶች
    • የቪዲዮ አምዶች
    • መፅሄቶች
  • ሃሳብ መስጫ
  • ዋና ገፅ
  • ቢሮው
    • ስለ እኛ
    • የቢሮ ሃላፊው መልዕክት
    • የስራ ክፍሎች
  • ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች
    • የቻናል አንድ ፕሮግራም
    • የተቀናጀ የበጀትና የወጪ መረጃ ሥርዓት (IBEX)
    • የፋይናንስ ግልፅነትና ተጠያቂነት (FTA)
  • ሰነዶች
  • ሚዲያ
    • አምዶች
    • የፎቶ አምዶች
    • የቪዲዮ አምዶች
    • መፅሄቶች
  • ሃሳብ መስጫ
No Result
View All Result
Harari BoFEC
ሃሳቦን ይስጡ
No Result
View All Result

በሀረሪ ክልል የመንግሥት ንብረት አስተዳደርን በዲጂታል ሥርዓት ለማዘመን የተደረገው ጥረት ወደ ተግባራዊ ምዕራፍ እየተሸጋገረ መሆኑ ተገለጸ

September 6, 2026
in መድረኮች, ስልጠናዎች, ወቅታዊ
0

በሀረሪ ክልል የመንግሥት ንብረት አስተዳደርን በዲጂታል ሥርዓት ለማዘመን የተደረገው ጥረት ወደ ተግባራዊ ምዕራፍ እየተሸጋገረ መሆኑ ተገለጸ

ሀረር፣ ነሀሴ 28/2018 (ገኢትቢሮ)፦ በሀረሪ ክልል ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የንብረት አስተዳደር ሥርዓት (DPMS) በግንባር ቀደምትነት ተግባራዊ ለማድረግ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ሃላፊ አቶ መሀመድ ያህያ ገለጹ።

ቢሮው ከ“አፍሮኔክስ ቴክ ሀብ” ጋር በመተባበር በክልሉ በሚገኙ 16 ተቋማት ላይ አዲሱን የዲጂታል ንብረት አስተዳደር ሥርዓት ሙሉ በሙሉ በሥራ ላይ ለማዋል ዐበይት ቅድመ ዝግጅቶችን አጠናቋል። የዚህ ተነሳሽነት አካል የሆነና ከእነዚሁ 16 ተቋማት ለተውጣጡ 53 ባለሙያዎችና ኃላፊዎች—የግዥ፣ ፋይናንስ፣ ንብረት አስተዳደር ኃላፊዎች እና የአይቲ ባለሙያዎች—ሲሰጥ የቆየው  በሁለት ዙር ተግባር ተኮር ሥልጠና በስኬት ተጠናቋል።

ተሳታፊዎች በስልጠናው ቆይታቸው የቋሚና አላቂ ንብረት ምዝገባ፣ ስልታዊ የንብረት ቆጠራ፣ የተሽከርካሪዎች መረጃ አያያዝ እንዲሁም የመሠረተ ልማት ምዝገባ ዳታቤዝ አጠቃቀም ላይ ጥልቅ ግንዛቤ አግኝተዋል። ሥልጠናው ተቋማት የመንግስት  ሀብት በጥራት፣ በብቃት እና በጥብቅ የቁጥጥር ማዕቀፍ ውስጥ እንዲመሩ የሚያስችል አቅም የሚፈጥር መሆኑ በመድረኩ ተመላክቷል።

በመዝጊያ መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ሃላፊ አቶ መሀመድ ያህያ፤ ይህ ሥልጠና ከዕለት ተዕለት የሥራ ልምምድ ወጣ ብሎ የሚከወን የተለመደ መድረክ ብቻ ሳይሆን የመንግሥትን ንብረት በዲጂታል ሥርዓት፣ በትክክለኛ መረጃ፣ በግልጽነትና በተጠያቂነት ለመምራት የተጀመረ ቁልፍ የለውጥ ምዕራፍ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። የመንግሥት ንብረት ኃላፊነት የአመራር ኃላፊነት ጭምር ነው ያሉት ሃላፊው በ16ቱ ተቋማት የትግበራ ሂደት ሲጀመር የተቋማት ኃላፊዎች አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ቢሮውም በበኩሉ በየሳምንቱ ተከታታይ ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የዲጂታል ሲስተም በራሱ ተአምር እንደማይሠራ የገለጹት አቶ መሀመድ ባለሙያዎች ትክክለኛ መረጃ በማስገባትና በኃላፊነት ስሜት ሲጠቀሙበት ብቻ ውጤት ሊመጣ እንደሚችል አሳስበዋል። ከሥልጠናው አዳራሽ ሲወጡ እውነተኛው ሥራ እንደሚጀምር በማስታወስ ሰልጣኞች የቀሰሙትን እውቀት ወደ መሬት አውርደው በተግባር በመተርጎም ለሥርዓቱ ስኬታማነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ አሳስበዋል።

በመድረኩ መገባደጃ ላይ በሥርዓቱ አጠቃቀም ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጎ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ ከተሰጠ በኋላ የዕውቅና የሰርተፊኬት ማረጋገጫ ተበርክቷል። በክልሉ በቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ በመረጃ የሚመራ፣ ቀልጣፋ እና ግልጽ የንብረት አስተዳደር ሥርዓት ለማስረፅ የተጀመረው ይህ ጉዞ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተረጋግጧል።

ShareTweetShare

ተመሳሳይ አመዶች

ብዝሃነትን ማክበርና በምክክር አንድነትን ማጠናከር ለጠንካራ የፌዴራል ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ።  ህዳር 4/2019 /ገኢትቢ/
ልዩ ልዩ

ብዝሃነትን ማክበርና በምክክር አንድነትን ማጠናከር ለጠንካራ የፌዴራል ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ። ህዳር 4/2019 /ገኢትቢ/

November 13, 2026
የሐረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በፕሮግራም በጀት ዝግጅት ዙሪያ ሥልጠና ሰጠ  ሐረር – ጥቅምት 19/2019
ስልጠናዎች

የሐረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በፕሮግራም በጀት ዝግጅት ዙሪያ ሥልጠና ሰጠ ሐረር – ጥቅምት 19/2019

October 31, 2026
የሀረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የ100 ቀናት ዕቅድ የ15 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ። – ጥቅምት 17/2019
ሌሎች

የሀረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የ100 ቀናት ዕቅድ የ15 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ። – ጥቅምት 17/2019

October 28, 2026
የሐረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የ2019 የመጀመሪያ ሩብ ዓመትና የ100 ቀናት ዕቅድ ዝግጅትን ገመገመ።
ሌሎች

የሐረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የ2019 የመጀመሪያ ሩብ ዓመትና የ100 ቀናት ዕቅድ ዝግጅትን ገመገመ።

October 9, 2026
በሐረሪ ክልል የመሠረታዊ አገልግሎቶችን ጥራትና ተጠያቂነት ለማጠናከር ያለመ የምክክር መድረክ ተካሄደ።
መድረኮች

በሐረሪ ክልል የመሠረታዊ አገልግሎቶችን ጥራትና ተጠያቂነት ለማጠናከር ያለመ የምክክር መድረክ ተካሄደ።

October 9, 2026
የሀረሪ ክልል የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በሰው ሐብት ትግበራ ፕሮግራም (Human Capital Operation)  የ2019 በጀት ዓመት የቅድመ ዝግጅት ውይይት አካሄደ።
መድረኮች

የሀረሪ ክልል የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በሰው ሐብት ትግበራ ፕሮግራም (Human Capital Operation)  የ2019 በጀት ዓመት የቅድመ ዝግጅት ውይይት አካሄደ።

October 3, 2026
Load More
Next Post
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ  የውይይት መድረክ  አካሄዷል።

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ  የውይይት መድረክ  አካሄዷል።

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

  • About
  • Help
  • Feedback
  • Contact
Call us: + 251 666 0955

Copyright @ 2022 HPRS Bureau of Finance and Economic Corporation , All Rights Reserved